Skip to main content
cerbornews1

በጥበብ ማገልገል ከተቋም ባለፈ ለኃገራዊ ዕቅድ መሳካት መሠረት መሆኑ ተገለጸ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ ቤት ለሰራተኞቹ የሰብዕና ግንባታ ስልጠና ሰጠ። ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ እንሴሱ በጊዜ መጣበብ እና በስራ ጫና ውስጥ ተሆኖ ይህን ስልጠና ማካሄድ ያስፈለገው ስብዕናው የታነፀ ሰራተኛ በጥበብ በማገልገል ለተቋማዊም ሆነ ለሀገራዊ እቅድ እውን መሆን ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው በመታመኑ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ፓስተር ቸርነት በላይ የስብዕና ግንባታ ስልጠናውን ሳቢ በሆነ መልኩ የሰጡት ሲሆኑ በስልጠናቸውም በታማኝነት እና በመልካም ሰብዕና ህዝብን ማገልገል ቤተሰብን እና ሀገርን መጠበቅ ነው። እንዲሁም በታማኝነት እና መልካም ስነ-ምግባር ማገልገል ለሀገራቸው መስዋትነት የከፈሉ እና ደማቸውን ላፈሰሱ ዜጎች ክብር መስጠት ነው ሲሉ አክለዋል። በማጠቃለያቸውም የሚያጓጉ እና የሚያማልሉ ማባበያዎች የተቋም አሰራር እና ህግን በማፋለስ ፍት አንዲዛባ ያደርጋሉ። በመሆኑም እነዚህን ማባበያዎችን በጥንካሬ ባለመቀበል የቤተሰብ እና የሀገር ህልውናን የሚያናጋ ድርጊት በመቆጠብ ሰራተኛው ሊሰራ እንደሚገባ በስልጠናቸው ገልፀዋል። (የገቢዎች ሚኒስቴር)