የተሻሻለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 199/2015 ዓ/ም መሰረት ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
1) የክልሉን የታክስና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በበላይነት ይመራል፣ ያስተዳድራል፤
2) በክልሉ በመካሄድ ላይ ያለውን የታክስ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም አፈጻጸም በባለቤትነት ይመራል፣ ያስተባብራል፤
3) ቀልጣፋ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ይዘረጋል፤
4) ለታክስ ከፋዩ አማራጭ የታክስ መክፈያ ተቋማትን ያመቻቻል፤
5) ታክስ ከፋዮች በፍቃደኝነት ታክስ የመክፈል ባህልን እንዲያዳብሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ተግባራዊ ያደርጋል፤
6) በክልሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ተመሰርቶ ጥናቶችን በማካሄድ የክልሉን የገቢ መሠረት ያሰፋል፣ በታክስ አስተዳደሩ የሚከሰቱ ችግሮች እንዲፈቱ ያደርጋል፣ የፖሊሲና የሕግ ሀሳቦችን ያመነጫል፤
7) የታክስ ሕጐችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ በማናቸውም ሰው እጅ የሚገቡ ሰነዶችን ይመረምራል፣ ይይዛል፤
8) ለታክስ አወሳሰን የሚያስፈልጉት መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያጠናክራል፣ እነዚህኑ በመጠቀም ታክስ ይወስናል፣ ይከሳል፤
9) ታክስ ያልሆኑ የከተማ ቦታ ይዞታ፣ የቤት ባለቤትነት፣ የንብረትና የአገልግሎት ክፍያ አወሳሰንና አሰባሰብ የሚያገለግሉ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
10) ከተሞች የማዘጋጃ ቤቶች ገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ጥናት ያደርጋል፣ ገቢዎችን በሕጉ መሠረት ይሰበስባል፣ ለመንግስት ግምጃ ቤት ገቢ ያደርጋል፣
11) የታክስ ወይም የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ የግብር ወይም የታክስ ከፋዬችን ንብረት በህግ መሠረት ያሰከብራል፣ ያስይዛል፣ በሃራጅ እንዲሸጥ ያደርጋል፣
12) በታክስ እና በግብር ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይመረምራል፣ ውሣኔ ይሰጣል፣ መቀጫዎችን በሕግ መሠረት ይጥላል፣ ያነሳል፣
13) ለግብር ይግባኝ ጉባዔ የሚቅረቡ የግብር ወይም የታክስ አወሳሰን ጉዳዮችን ይከታተላል ያስወስናል፣
14) ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡