ተቋሙ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
የመደበኛ ግብር ከፋዮች ምዝገባ ማከናወን፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ማከናወን፣
በታክስ መልዕክተኛ አማካይነት የዕለት ገቢ ግመታ መረጃ መሰብሰብና ግብር /ታክስ በግምት መወሰንና ማስታወቅ፣
አዳዲስና የደረጃ ለውጥ ያደረጉ የንግድ ድርጅቶችን ግብር/ታክስ መወሰንና ማስታወቅ፣
ከሶስተኛ ወገን በተገኘ መረጃ መሠረት ግብር/ታክስ መወሰንና ማስታወቅ፣
በኦዲት ግኝት መረጃ መሠረት ግብር/ታክስ መወሰንና ማስታወቅ፣
የደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ካላቀረቡ ወይም ገቢያቸውን ካላስታወቁ የሚፈለግባቸውን ግብር/ታክስ በግምት መወሰንና ማስታወቅ፣
ከግል ንግድ ድርጅቶች እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅት ተቀጣሪዎች የደመወዝ ገቢ ግብር መወሰንና መሰብሰብ፣
የኪራይ ገቢ ግብር/ታክስ መወሰንና ማስታወቅ፣
የደመወዝ ገቢ ግብር መሰብሰብ፡
የመደበኛ የንግድ ትርፍና የማዘጋጀት ቤት ግብር መሰብሰብ፣
የማዘጋጃ ቤት የአስተዳደርና የአገልግሎት ክፍያ መሰብሰብ፡
የተርን ኦቨር ታክስ መሰብሰብ፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ መሰብሰብ፡
የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር መወሰንና መሰብሰብ፡፣
ከእርሻ ኢንቨስተሮች የመሬት ኪራይ እና የእርሻ ሥራ ትርፍ ገቢ ግብር መሰብሰብ፣
ከጫት፣ ከሌሎች የግብርና ምርት ውጤቶች እና ከተፈጥሮ ሀብት ውጤቶች ገቢ መሰብሰብ፣
ውክልና ከተሰጣቸው ድርጅቶችና ከተከፋይ ሂሳብ ተቀናሽ 2% ቅድመ ግብር እና የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ከተጠቃሚዎች መሰብሰብና ለባለመብቶች ማስተላለፍ፣
የቴምብር ቀረጥ መሸጥና ገቢ መሰብሰብ፣
ውዝፍ ዕዳ መሰብሰብ፣
ውዝፍ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር መሰብሰብ፣
ቋሚ የንግድ አድራሻ ሳይኖራቸው ተዘዋውረው ከሚነግዱ ግለሰቦች ግብር/ታክስ በቁርጥ መሰብሰብ፣ ለግብር ከፋዮች የአከፋፈል ማስረጃ መስጠት፣
ከመደበኛ ግብር ከፋይነት እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ለመውጣት የስረዛ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ተገልጋዮች ምላሽ መስጠት፣
ለደረሰኝ ሕትመት ጥያቄ ፈቃድ መስጠት፣
ከመንግሥት ልማት እና ከግል ድርጅቶች የጡረታ መዋጮ መሰብሰብ፣
የክፍያ ጊዜ ገደብ መፍቀድ እና መቀጫ የማንሳት ጥያቄ ምላሽ መስጠት፣
የንብረት ባለቤትነት ስም ዝውውር ጥያቄ ለሚያቀርቡ ተገልጋዮች ተገቢውን ግብር/ታክስ በማስከፈል የማስረጃ /ክሊራንስ አገልግሎት መስጠት/፣
የብልጫ ክፍያ ተመላሽ ጥያቄን ተቀብሎ ማስተናገድ፣
የተቆርቋሪ ወገኖች ጥቆማ የመቀበልና የኢንተለጀንስ መረጃ በመሰብሰብ ግኝቶችን መለየት፣
የግብር ከፋዮች የሂሣብ መዝገቦችንና ሠነዶችን ኦዲት ማድረግ፣
የግብር ከፋዮች ማኀደር መመርመር፣
የሦስተኛ ወገን የታክስ መረጃ መሰብሰብና ማሠራጨት፣
በግብር እና በታክስ ላይ የሚነሱ አቤቱታዎችን በመመርመር ውሣኔ መስጠት፣
የታክስ ወንጀል መመርመርና ክስ መመስረት፣
የግብር ይግባኝ ክርክር ማድረግ፣
ባለድርሻ አካላትንና ተገልጋዩ ሕብረተሰብን በማሳተፍ የጥናት ሠነድ ማዘጋጀት፣
ባለድርሻ አካላትንና ተገልጋዩን ሕብረተሰብ በማሳተፍ ተወዳዳሪና ተራማጅ የታክስ ማዕቀፍ መቅረጽ፣
በፈቃደኝነት ግብር የመክፈል ባህል ያዳበረ ግበር ከፋይ ለመፍጠር የታክስ/የግብር ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ስልጠና መስጠት፣
የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ጥራቱን የጠበቀ የከተሞች የንብረት ግብርና የአገልግሎት ክፍያ መመሪያ (ደንብ) ማዘጋጀትና በሥራ ላይ ማዋል፣
የማዘጋጃ ቤቶች የገቢ መጣኔ መሰፈርት ሰነዶችን ማዘጋጀትና በሥራ ላይ ማዋል፣
ተገልጋዩና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የገቢ መጣኔ የጥናት ሰነዶች ማዘጋጀት፣
ጥራት ያለው የገቢ መጣኔ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና በሚመለከታቸው አካላት በማፀደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣
የገቢ መጣኔ ደንቦች ማዘጋጀትና በከተሞች ም/ቤቶች በማፀደቅ