Skip to main content
11

የሪፎርም ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለአመራርና ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ሪፎርም ተቋማትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለተቋሙ አመራርና ሠራተኞች በቡታጅራ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። የስልጠናው ዋና ዓላማ በክልሉ በተጀመረው የሪፎርም ሥራ ላይ የአመራሮችና የሠራተኞችን ግንዛቤ በማሳደግ፣ የመንግስት አገልግሎትን ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ተጠያቂና ውጤታማ በማድረግ የሚያስችሉ የአሠራር ለውጦችን በተግባር ለማስፈፀም የሚያስችል አቅም መገንባት ነው። በስልጠናው መክፈቻ መርሃ ግብር የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች እና የተቋሙ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በስልጠናው የተለያዩ የሪፎርም ጉዳዮች በስፋት እየቀረቡ ሲሆን፣ በተለይም የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ፣ የሪፎርም ፍኖተ ካርታ ይዘቶች፣ የተግባር ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ዝርዝር ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል። በስልጠናው የተገለጸው መንግስት በሀገር ደረጃ የጀመረው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዋና ዓላማ ወጥነት ያለው የአሠራር ሥርዓት በመፍጠር፣ የመንግስት ተቋማት ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ተጠያቂ እና ለዜጎች ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል መሆኑ ነው። ይህም በተቋማት ውስጥ የተሻለ የአፈፃፀም ባህል በመፍጠር ውጤታማ አገልግሎትን ለማረጋገጥ ያግዛል። ስልጠናው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ የሪፎርም ጉዳዮች ዋና አማካሪ በአቶ ብሩክ ቁምላሪ እና በአቶ ፍትሕአወቅ ፋንታሁን እየተሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች በሪፎርሙ አተገባበር ላይ ያላቸውን ጥያቄዎችና ልምዶች በማካፈል ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ። መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የተቋሙን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል፣ የሪፎርም ሥራዎችን በውጤታማነት ለመተግበር እና ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ይታመናል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ገቢዎች ቢሮ Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau Central Ethiopia Region Urban Development and Construction Bureau 

#ለተጨማሪ_መረጃዎች👇👇👇👇👇 

👉የፌስቡክ ገፅ https://www.facebook.com/profile.php?id=61562204634443 

👉የቲክቶክ ገፅ https://www.tiktok.com/@central.ethiopia4... 

👉የዩቲዩብ ገፅ (https://youtube.com/@centralethiopiarevenuebureau... 

👉ኢንስታገራም https://www.instagram.com/centralethiopiarevenue... 

👉በሬዲዮ ፕሮግራም በDebub Fm100.9 ሬዲዮ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ8:40_9:00 ይከታተሉን 

👉#በነፃ_የስልክ_መስመር_6087 ይደውሉ ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !! See less